ስለ ትራንስሊንክ (TransLink)

በመላው ደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ የኣውቶቡስ ፣የባቡር፣የጀልባና የቀላል ባቡር(ትራም) ኣገልግሎት እንዲሁም በኬንስ ውስጥ በትሮፒካል ሰሜናዊ ክዊንስላንድ የኣውቶቡስ ኣገልግሎት እናስተባብራለን ፤ እናቀርባለንም።

በተጨማሪም ለደንበኞች መረጃ የመስጠት ቲኬት የመቁረጥና የመገናኛ ኣውታር የመዘርጋት ሃላፊነትም ኣለብን።

የኣገልግሎት ኣድማሳችን

ደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ

ትራንስሊንክ (TransLink) በደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ በ፳፫/23 ቀጠናዎችና ፯/7 ኣካባቢዎች ውስጥ ኣገልግሎቱን ይሰጣል። የደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ መገናኛ ኣውታራችን ከሰሜን ጊይምፒ ጀምሮ እስከ ደቡብ ኩሉንጋታ እንዲሁም እስከ ምዕራብ ሄሊደን የተዘረጋ ነው።

ኬንስ (Cairns)

የኬይንስ የመገናኛ ኣውታራችን ማለት በኬይንስ ከባቢያዊ ምክር ቤት ስር ያሉትን ቦታዎች ሁሉ ያካተተ ነው። ይሄም የተዘረጋው ከሰሜን ፓም ኮቭ ፣ ከደቡብ እስከ ጎርደንቬል፣በምዕራብ ሬድ ሊንች እንዲሁም የኬይን ከተማና በኣካባቢው የሚገኙትን ቀበሌዎችን ያካትታል።

ኣገልግሎት የምንሰጥባቸው ኣካባቢዎች

የጉዞ መረጃዎች

ትራንስሊንክ (TransLink) ማለት ሰዎችና ቦታዎችን የማገናኘት ጉዳይ ነው።

እርስዎ ጎብኚም ሆኑ ነዋሪ በደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድና ኬይንስ በህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅመው የትም ቦታ ለመድረስ በጣም ቀላል ነው።

ኣገልግሎቶችና የጊዜ ሰሌዳዎች

የኣውቶቡስ ፣የባቡር፣የጀልባና የቀላል ባቡር ኣገልግሎቶችን በተመለከተ የተዘጋጁ የጊዜ ሰሌዳዎችካርታዎች ፣ የመዳረሻ መረጃዎች እንዲሁም ስለ ቲኬትና ዋጋን ቲኬቶችና ዋጋዎች ኣስመልክቶ የምትፈልጉትን ማናቸውም መረጃ እንዲሁም ኣውቶቡስ ባቡር ጀልባ ወይም ትራም እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ የሚያሳየውን‘how to’ በየሚለውን መመሪያ ማግኘት ይችላሉ።

በተጨማሪም ስለሚከተሉት ጉዳዮችም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የጉዞ ማቀጃ

ጉዞዎን ለማቀድ የጉዞ ማቀጃ (journey planner)ን ይጠቀሙ

የመንገዱን ቁጥርና ስም በማስገባት (ለምሳሌ 16 Smith Street) ብለው ቀበሌውን (suburb)ን በሚለው ቦታ ላይ ይምሉ። ወይም ደግሞ የሆነ ታዋቂ ቦታ ወይም የኣውቶቡስ፣ የባቡር ወይም የትራም ማቆሚያ ወይም የጀልባ ማረፊያውን መሙላት ይቻላል ለምሳሌ ጋባ፣ ብሪዝቤን ኣየር ማረፊያ፤ ኬይን የገበያ ማእከል ወይም ኤኖጌራ ጣቢያ።

ክዊንስላንድን መጎብኘት

ደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድን መጎብኘት

እንደ seeQ cardGold Coast go explore cardgo card ወይም single paper ticket የመሳሰሉትን በመጠቀም የደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ የመገናኛ ኣውታር በመጠቀም በትራንስሊንክ መጓዝ ይችላሉ።

የ go card ዋጋ ከኣንድ ወረቀት ቲኬት ዋጋ በ30% የህል የረከሰ ነው። ስለ ወቅታዊ የጉዞ ዋጋና (current fares)ቅናሾች (concessions) እና ቅናሾችና የቁጠባ መንገዶች (discounts and ways to save) ተጨማሪ ያንብቡ።

seeQ card ደቡብ ምስራቅ ክዊስላንድን እየዞሩ ለማየት የሚያመች ቀላሉ መንገድ ነው። በseeQ card ለ3 ወይም 5 ቀናት ያህል በማንኛውም TransLink ኣገልግሎቶች መጠቀም ይችላሉ። ስለ seeQ card ተጨማሪ ያንብቡ።

Gold Coast go explore card ለጎልድ ኮስትን ጎብኝዎች ተመራጭ ካርድ ነው። ኣንድ ቲኬት በመግዛት ቀኑን ሙሉ እንደፈለጉ በኣውቶቡስና በባቡር በጎልድ ኮስት ውስጥ ብቻ ወደ ተለያዩ ፓርኮች፣ ጎልድ ኮስት ኣየር ማረፊያ የመሳሰሉት ኣገልግሎቶች መሄድ ይቻላል። Gold Coast go explore cardስለሚለው በተጨማሪ ያንብቡ።

ኬንን መጎብኘት

የነጠላ የቀን ወይም የሳምንት Cairns paper ticket በመግዛት መጓዝ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎትን tickets, fares and zones in Cairns የሚለውን ይመልከቱ።

ቲኬቶችና ዋጋዎች

ቲኬቶች፣ ዋጋዎችና የደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ ቀጠናዎች

የቲኬት ዓይነቶች

ጎብኚ ከሆኑ የትራንስሊንክ ኣገልግሎት go cardን በመጠቀም ደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድን መጎብኘት ይችላሉ። seeQ card ወይም Gold Coast go explore card (በጎልድ ኮስት ውስጥ ለኣውቶቡስና ለትራም ተጠቃሚዎች) ለኣንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የወረቀት ቲኬትም መግዛት ይችላሉ።

go card (ጎ ካርድ)

go card የኤሌክትሮኒክ ካርድ ሲሆን ትራንስ ሊንክ በሚሰጣቸው የኣውቶቡስ፣ የባቡር፣ የጀልባና በኤሌትሪክ የሚሰራ ትራም እንደፈለጉ በመሻገር በደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ በሙሉ መጓዝ ይችላሉ።

ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነ፣ ሂሳቡን በሰለጠ መንገድ የሚያሰላና የተለያዩ የመጓጓዣ ዘዴዎች መሻገሩን ጨምሮ ብዙ ሰው በማይጓዝበት ሰዓት ለሚጓዙና ብዙ ጊዜ ደጋግመው ለሚጓዙ ሰዎች የሚገባቸውን የዋጋ ቅናሽ በማስላት ሂሳብዎን ከካርድዎ ቀንሶ ያስከፍላል።

በቅርብዎ ካለው የgo card ጣቢያ ወይም auto top up የሚባለውን ኣጠቃቀም ካዘጋጁ ለጉዞዎ በቂ የሆነ ገንዘብ መጨመር ያስችልዎታል።

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎትን በgo card terms and conditions ያለውን የኣጠቃቀም የውል ስምምነት ያንብቡ።

የ go card አጠቃቀም

ወደ ኣውቶቡስ ወይም ወደ ጀልባ በሚሳፈሩበት ጊዜ የካርድዎን ገፅ በማንበቢያው ላይ ማስነካት ይገባዎታል። በሚወርዱበትም ጊዜ በተመሳሳይ ካርድዎን ማስነካት ይጠበቅብዎታል።

ወደ ሌላ ኣውቶቡስ፣ ወይም ባቡር ወይም ጀልባ ወይም ትራም ኣገልግሎት በሚቀይሩበት ጊዜ በተመሳሳይ ካርድዎን በማንበቢያው ላይ ማስነካት ይጠበቅብዎታል። በተሳፈሩበት የባቡር ጣቢያ ላይ ሌላ ባቡር የሚቀይሩ ከሆነ ግን ማስነበብ ኣይጠበቅብዎትም።

መብራቶችን ይመልከቱ የምልክት ድምፆችንም ያዳምጡ

 • ለኣዋቂዎች ኣረንጓዴ መብራት ፩ የምልክት ድምፅ
 • ለህፃናት ለኣዛውንቶች፣ቅናሽ ለተደረገላቸው ቢጫ መብራትና ፪ የምልክት ድምፅ

ትክክለኛውን የጉዞ ሂሳብ በቀጥታ ከካርድዎ ከቀነሰ በኋላ ካርድዎን በሚያነሱበት ጊዜ በካርዱ ውስጥ ያልዎትን ቀሪ ገንዘብ በማንበቢያ ሰሌዳው ላይ ያሳይዎታል።

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎትን በ go card ያለውን ዝርዝር ማብራሪያ ያንብቡ።

go card ዎን የት እንደሚገዙና ሂሳብዎን የት እንደሚሞሉ

go card በሚከተለው መንገድ መግዛት ይችላሉ

 • በኢንተርኔት መስመር ላይ (online)
 • በማንኛውም የ 7-Eleven የነዳጅ ማደያ
 • በባቡር ጣቢያ የቲኬት መሸጫዎች
 • በኣውቶቡስና የትራም ጣቢያዎች ባትው የቲኬት መሸጫ ማሽኖች
 • እንደ newsagentና የመሳሰሉ ኣንዳንድ እቃ መሸጫ ኣንስተኛ ሱቆች

በቅርብዎ የሚገኘውን ጣቢያ nearest location ለማወቅ በስልክ ቁጥር 13 12 30 በማንኛውም ሰዓት 24 ሰዓታት ፣ በሳምንት7 ቀናት መደወል ይችላሉ።

ነጠላ የወረቀት ቲኬት

ነጠላ የወረቀት ቲኬት (single paper ticket) በተደጋጋሚ የህዝብ ትራንስፖርት ለማይጠቀሙ በደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ ባሉት የኣውቶቡስ የባቡር የጀልባና የትራም የትራንስፖርት ኣገልግሎት ለሚጠቀሙ ተጓዦች ለኣንድ ጊዜ ጉዞ የሚያገለግል ቲኬት ነው። ቲኬቱን በኣውቶቡስና በጀልባ ላይ ሲሳፈሩ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለባቡርና ለትራም ግን በየጣቢያዎቻቸው መግዛት ይችላሉ።

የቲኬት ዋጋዎች

በደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ በሚጓዙበት ጊዜ ሂሳብዎን ለማስላት በሚጓዙበት ጊዜ ኣቋርጠው የሚያልፉባቸውን ቀጠናዎችን ይመልከቱ። ከከፍተኛው ቀጠና ኣንስተኛውን ቀጠና ከቀነሱ በኋላ ኣንድ ይጨምሩ። ይህ ስሌት እርስዎ በትክክል የሚጓዙባቸውን ቀጠናዎችን ኣስልቶ የሚያስከፍል ቀመር ነው። በተጨማሪምjourney planner በመጠቀም መጓዝ ለሚፈልጉት የጉዞ ሂሳብ ማስላት ይችላሉ።

ቀጠናዎች

ትራንስሊንክ በደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ 23 ቀጠናዎች ውስጥ ኣገልግሎቱን ይሰጣል። ዋጋዎች የሚተመኑት በኣዋቂ ወይም በተደጓሚ ተሳፋሪዎችና ተጓዦች ወደ መዳረሻችሁ እስክትደርሱ ኣቋርጣችሁ የምትሄዱባቸውን ቀጠናዎችን ባገናዘበ መልኩ ነው።

የቀጠናው ኣሰራር የቀለበት ገፅታ ያለው ሲሆን ከብሪዝቤን የቢዝነስ ማእከል ቀጠና ፩ ጀምሮ ወደ ሰሜን ሳንሻይን ኮስት ጂምፒ፣ ወደ ደቡብ ጎልድ ኮስት በምዕራብ ደግሞ ወደ ምዕራብ ሄሊደን የሚያመራ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ወቅታዊ የጉዞ ዋጋና (current fares) የቀጠናዎች የጉዞ ዋጋን (fare zones) በሚመለከት ይመልከቱ።

ቲኬቶች የጉዞ ዋጋዎችና ቀጠናዎች በኬንስ

በኬንስ ነጠላ ዕለታዊና ሳምንታዊ ቲኬቶች ኣውቶቡስ ውስጥ በሚሳፈሩበት ጊዜ ሊቆርጡ ይችላሉ።

የጉዞ ዋጋዎች የሚሰሉት በሚያቋርጡባቸው ቀጠናዎች ብዛት ነው። በኬንስ ፲፩ ቀጠናዎች ኣሉ ። የገበያ ማዕከሉ (CBD) ልዩ ቀጠና (20) ሲሆን ወደ ሰሜን ፓም ኮቭ ወደ ደቡብ ጎርደን ቬል እና ወደ ምዕራብ ሬድሊንች ድረስ የተዘረጋ ነው።

ትክክለኛውን የቀጠናዎች ብዛትና ዋጋ ለማወቅ ፤ እባክዎትን የኬንስ የመገናኛ ኣውታር ካርታ ያለውን የቀጠና የጉዞ ዋጋ ቀመርና (fare zone calculator) እንዲሁም ወቅታዊ የጉዞ ዋጋ (current fares) ይመልከቱ፣

ኣጠቃቀም

የኣውቶቡስ ኣጠቃቀም

ከመጓዝዎ በፊት

ኣውቶቡስ ውስጥ መሳፈር

 • ሾፌሩ ሊያይዎት በሚችል የኣውቶቡሱ ማቆሚያ ቦታ ላይ ይቁሙ።
 • መሳፈር የሚፈልጉ መሆንዎን ለማሳወቅ እጅዎን ከፍ ኣርገው ለሾፌሩ ምልክት ይስጡ።
 • go card, seeQ card ወይም Gold Coast go explore card ይግዙ (በጎልድ ኮስት ብቻ በኣውቶቡስና በትራም ለመጓዝ) ከመሳፈርዎ በፊት ቲኬት ወይም ትክክለኛውን ገንዘብ ማዘጋጀት ይጠበቅብዎታል።
 • በቅናሽ ዋጋ (concession fare) የሚጓዙ ከሆነ የተፈቀደልዎት የቅናሽ ካርድ (concession entitlement card) መያዝዎን ያረጋግጡ
 • በሚሳፈሩበት ጊዜ go card, seeQ card ወይም Gold Coast go explore card ዎን በኣውቶቡሱ ውስጥ በሚገኘው የካርድ ማንበቢያ ሰሌዳ ላይ ያስነብቡ ወይም ቀደም ብለው የገዙትን ቲኬት ለሾፌሩ ያሳዩ ወይም ደግሞ ሲሳፈሩ መግዛት ይችላሉ። ቲኬት እንዴት መግዛት እንደሚችሉ በ how to buy a ticket ይመልከቱ።
 • ለወራጆች ቅድሚያ ይስጡ።
 • ኣንዳንድ የኣውቶቡስ ኣገልግሎት ሰጪዎች የቅድሚያ ክፍያ pre-paid የሚጠይቁ ሲሆን እነሱም የ‘P’ ምልክት በመንገዱ/መስመሩ ፊት ለፊት ያስቀምጣሉ። በነዚህ ኣውቶቡሶች ለመጠቀም የgo card, seeQ card ወይም ቀደም ብሎ የተገዛ የወረቀት ቲኬት (pre-purchased paper ticket)መግዛት ይጠበቅብዎታል። go card ወይም seeQ card የያዙ ሰዎች ከፊትም ሆነ ከኋላ መግባት ይችላሉ። የወረቀት ቲኬት የያዙ ተሳፋሪዎች ግን በፊት በር ብቻ ነው መግባት የሚችሉት።

የኣውቶቡስ ጉዞ

 • ከተሳፈሩ በኋላ ወደ ኋላ ሄደው ይቀመጡ። መቀመጫ ከሌለ ኣውቶቡሱ ላይ ከተገጠመው ቋሚ መያዣ ወይም የደህንነት መከላከያ ይዘው ይቁሙ።
 • ምን ጊዜም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ሰዎች ማለትም የኣካል ጉዳት ላለባቸው፣ ለኣዛውንቶች፣ ለነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ትናንሽ ህፃናት ለያዙ ወላጆች መቀመጫ መልቀቅ ኣስፈላጊ ነው።
 • ከኣውቶቡሱ ለመውረድ ከፈለጉ ቢያንስ ከ፩፻ ሜትር በፊት ደወሉን ይደውሉ። የሚወርዱበትን ቦታ የማያውቁ ከሆነ በሚሳፈሩበት ጊዜ ሾፌሩን ይጠይቁ።
 • በሚወርዱበት ጊዜ በተቻለ መጠን በኋለኛው በር ለመውረድ ይሞክሩ።
 • በሚወርዱበት ጊዜ go card, seeQ card ወይም Gold Coast go explore card (በጎልድ ኮስት ብቻ በኣውቶቡስና በትራም የሚጓዙበትን) በካርድ ማንበቢያ ሰሌዳ ላይ ካርድዎን ያስነብቡ ።
 • ወደ ሌላ ኣውቶቡስ፣ ጀልባ ወይም የትራም ኣገልግሎት በሚሳፈሩበትም ጊዜ ሆነ በሚወርዱበት ካርድዎን ማስነበብዎን ያረጋግጡ።
 • የትራንስሊንክ የጉዞ ሁኔታ conditions of travel ይመልከቱ።

የባቡር ኣጠቃቀም

ከመጓዝዎ በፊት

ባቡር ውስጥ መሳፈር

 • በባቡር ጣቢያው መጠበቂያ ስፍራ ወይም መግቢያ ላይ ባለው የካርድ ማንበቢያ ሰሌዳ ላይ የgo card ዎን ወይም seeQ card ዎን በማስነካት ያስነብቡ፣ የገዙትን ቲኬት ለጣቢያው ኣለቃ ወይም ለቲኬት መኮንኑ ያሳዩ ወይም ቲኬት ይግዙ ። ቲኬት ለመግዛት how to buy a ticket ይመልከቱ
 • በቅናሽ ዋጋ የሚጓዙ ከሆነ፤ የተፈቀደልዎትን የቅናሽ ዋጋ ካርድ መያዝዎን ያረጋግጡ።
 • በባቡር መጠበቂያ ስፍራ ላይ ባቡር በሚጠብቁበት ወቅት ሁሌም ከቢጫ መስመሩ በስተኋላ ሆነው ይጠብቁ።
 • ለወራጆች ቅድሚያ ይስጡ።

በባቡር በሚጓዙበት ጊዜ

 • እንደተሳፈሩ ከመተላለፊያውና ከበሩ ወዲያውኑ ይልቀቁ።
 • መቀመጫ ከሌለ ባቡሩ ላይ ከተገጠመው ቋሚ መያዣ ወይም የደህንነት መከላከያ ይያዙ።
 • ምን ጊዜም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ሰዎች ማለትም የኣካል ጉዳት ላለባቸው፣ ለኣዛውንቶች፣ ለነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ትናንሽ ህፃናት ለያዙ ወላጆች መቀመጫ መልቀቅ ኣስፈላጊ ነው።
 • በሚወርዱበት ጊዜ go card ወይም seeQ card ዎን ሰሌዳ ላይ ካርድዎን ያስነብቡ ።
 • ወደ ሌላ ኣውቶቡስ፣ ጀልባ ወይም የትራም ኣገልግሎት በሚሳፈሩበትም ጊዜ ሆነ በሚወርዱበት ካርድዎን ማስነበብዎን ያረጋግጡ።
 • የትራንስሊንክ የጉዞ ሁኔታ (conditions of travel) ይመልከቱ።

የጀልባ ኣጠቃቀም

ከመጓዝዎ በፊት

ጀልባ ውስጥ መሳፈር

 • በጀልባው ማቆሚያ የግራ በኩል ላይ ከተሰለፉ ወራጆች በቀኝ በኩል በቂ መተላለፊያ ይኖራቸዋል።
 • ለወራጆች ቅድሚያ ይስጡ።
 • የጀልባው ኣዛዥ ለመሳፈር ዝግጁ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ ወደ ጀልባው ይሳፈሩ።
 • ወደ ጀልባው በሚሳፈሩበት ጊዜ በጀልባው ውስጥ ባለው የካርድ ማንበቢያ ሰሌዳ ላይ የgo card ዎን ወይም seeQ card ዎን በማስነካት ያስነብቡ፣ የገዙትን ቲኬት ለጣቢያው ኣለቃ ወይም ለቲኬት መኮንኑ ያሳዩ ወይም ቲኬት ይግዙ ። ቲኬት ለመግዛት how to buy a ticket ይመልከቱ

በቅናሽ ዋጋ የሚጓዙ ከሆነ፤ የተፈቀደልዎትን የቅናሽ ዋጋ ካርድ መያዝዎን ያረጋግጡ።

በጀልባ መጓዝ

 • እንደተሳፈሩ ውስጥ መቀመጥ ይችላሉ ወጭ ከፈለጉም በተፈቀደው ቦታ ላይ መሆን ይችላሉ።
 • መቀመጫ ከሌለ ጀልባው ላይ ከተገጠመው ቋሚ መያዣ ወይም የደህንነት መከላከያ ይያዙ።
 • ምን ጊዜም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ሰዎች ማለትም የኣካል ጉዳት ላለባቸው፣ ለኣዛውንቶች፣ ለነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ትናንሽ ህፃናት ለያዙ ወላጆች መቀመጫ መልቀቅ ኣስፈላጊ ነው።
 • እንደ መውረጃዎ ሁኔታ ከፊትም ሆነ ከኋላ የጀልባው በር መውጣት ይችላሉ- ማስታወቂያም ይነገርዎታል።
 • ከጀልባው በሚወርዱበት ጊዜ go card ወይም seeQ card ዎን ማንበቢያ ሰሌዳው ላይ በማስነካት ካርድዎን ያስነብቡ ።
 • ወደ ሌላ ኣውቶቡስ፣ ጀልባ ወይም የትራም ኣገልግሎት በሚሳፈሩበትም ጊዜ ሆነ በሚወርዱበት ካርድዎን ማስነበብዎን ያረጋግጡ።
 • የትራንስሊንክ የጉዞ ሁኔታ (conditions of travel) ይመልከቱ።

የትራም ባቡር ኣጠቃቀም

ከመጓዝዎ በፊት

 • ጉዞዎን ያቅዱ (Plan your journey)
 • ትራሞች ፀጥ ያሉ ናቸው-ኣካባቢዎን ያገናዝቡ
 • ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 13 12 30 ደውለው ይጠይቁ

ወደ ትራም ሲሳፈሩ

 • በሚሳፈሩበት ጊዜ go card, seeQ card ወይም Gold Coast go explore card ዎን (ለትራምና ለኣውቶቡስ ጉዞ በጎልድ ኮስት ብቻ) በትራም ጣቢያው መጠበቂያ በሚገኘው የካርድ ማንበቢያ ሰሌዳ ላይ ያስነብቡ ወይም ነጠላ የወረቀት ቲኬት ይግዙ። እንዴት መግዛት እንደሚችሉ በ how to buy a ticket ይመልከቱ።
 • በቅናሽ ዋጋ የሚጓዙ ከሆነ፤ የተፈቀደልዎትን የቅናሽ ዋጋ ካርድ መያዝዎን ያረጋግጡ።
 • በትራሙ መጠበቂያ ስፍራ ላይ ትራሙን በሚጠብቁበት ወቅት ሁሌም ከቢጫ መስመሩ በስተኋላ ሆነው ይጠብቁ።
 • ለወራጆች ቅድሚያ ይስጡ።

በትራም መጓዝ

 • እንደተሳፈሩ ከመተላለፊያውና ከበሩ ወዲያውኑ ይልቀቁ።
 • መቀመጫ ከሌለ ባቡሩ ላይ ከተገጠመው መያዣ ወይም የደህንነት መከላከያ ይያዙ።
 • ምን ጊዜም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ሰዎች ማለትም የኣካል ጉዳት ላለባቸው፣ ለኣዛውንቶች፣ ለነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ትናንሽ ህፃናት ለያዙ ወላጆች መቀመጫ መልቀቅ ኣስፈላጊ ነው።
 • በሚወርዱበት ጊዜ go card, seeQ card ወይም Gold Coast go explore card ዎን (ለትራምና ለኣውቶቡስ ጉዞ በጎልድ ኮስት ብቻ) በትራም ጣቢያው መጠበቂያ በሚገኘው የካርድ ማስንበቢያ ሰሌዳ ላይ ያስነብቡ።
 • ወደ ሌላ ኣውቶቡስ፣ ጀልባ ወይም የትራም ኣገልግሎት በሚሳፈሩበትም ጊዜ ሆነ በሚወርዱበት ካርድዎን ማስነበብዎን ያረጋግጡ።
 • የትራንስሊንክ የጉዞ ሁኔታ (conditions of travel) ይመልከቱ።

የማዕበል መቅዘፊያ (surfboard) ማስቀመጫ ኣጠቃቀም

 • በትራሙ ወስጥ የሚገኘው የማዕበል መቅዘፊያ ማስቀመጫ ከፍታ ጣሪያ ፮ ጫማ ነው
 • የማዕበል መቅዘፊያ ማስቀመጫ ሰረገላ/መጫኛ የሚገኘው በትራሙ መሃል ኣካባቢ ነው። እነዚህ ሰረገላዎችን የሚጠቁም በሩ ኣካባቢ የተለጠፈው ማስታወቂያ ይመልከቱ።
 • በሚሳፈሩበት ወቅት መቅዘፊያዎን ወደሚያስቀምጡበት ሰረገላው ጠጋ በሚል ትራም ላይ ቢሳፈሩ መልካም ነው ምክንያቱም ፈጠን ብለው መደ መቅዘፊያዎ መድረስ እንዲችሉ።
 • ወደሚፈልጉብት ቦታ እስኪደርሱ የማዕበል መቅዘፊያዎን በማስቀመጫው ቦታ በጥንቃቄ መቀመጡን ያረጋግጡ።

ያግኙንና ይርዱን

የትራንስሊንክ ጉዳይ ስዎችና ቦታዎችን ስለማገናኘት ነው። እርዳታ ለመጠየቅ ወይም ኣስተያየት ለመስጠት ቀጥለው በተመለከቱት መገናኛዎችን ይመልከቱ፡

በድረገፅ መስመር

ኣስተያየት ለመስጠትም ሆነ ጥያቄ ለመጠየቅ የድረገፅ መስመር ቅፃችን (online form) ይመልከቱ።

ለኣሁንም ሆነ በቀጣይነት ለሚኖሩት የኣውቶቡስ፣ ባቡርና፣ ጀልባና ትራም ወቅታዊ መረጃዎች (service updates) ይመልከቱ።

የግል ሚስጢርን በሚመለከት (Privacy statement)
ስለ go card ሲፈልጉ ቅፅ ሞልተው ከሚልኩልን በቀጥታ ይደዉሉልን። ከግል ሚስጢር ኣጠባበቅ መመሪያ ጋር በተያያዘ ብቻዎትን ማነጋገር እንፈልጋለን።

ስልክ

 • በቤትዎ ስልክ በ13 12 30 ይደውሉልን። በ13 ወደሚጀምር ቁጥር ከየትም የኣውስትራሊያ ክፍል ቢደውሉ የሚከፍሉት ዋጋ የተወሰነ ነው። ከሞባይል ሲደውሉ ግን ዋጋውን ከፍ ያለ ነው።
 • ከውጭ ኣገር ለሚደውሉ +61 7 3851 8700 ይደውሉ።
 • እንግሊዝኛ ተናጋሪ ላልሆኑ ፡ በ13 12 30 ደውለው ኣስተርጓሚ በመጠቀም የሶስትዮሽ ውይይት ማድረግ ይችላሉ።
 • ብሄራዊ የቅብብሎሽ ኣገልግሎት/ National Relay Service (የመስማት ወይም የመናገር ችግር ካለብዎት) TTY: በ13 36 77 ደውለው ወደ 13 12 30 እንዲያገናኝዎት ይጠይቁ።
 • መናገርና ማዳመጥ (ከንግግር - ወደ ንግግር- ቅብብሎሽ) በ1300 555 727 ደውለው ወደ 13 12 30 እንዲያገናኝዎት ይጠይቁ።
 • የኢንተርኔት ቅብብሎሽ፡ ወደ ብሄራዊ የቅብብሎሽ ኣገልግሎት ከተገናኙ በኋላ ወደ 13 12 30 እንዲያገናኝዎት ይጠይቁ።

ስለሚፈልጉት ኣጠቃላይ የህዝብ ኣገልግሎት እኛን መጠየቅ የሚገባዎት ሲሆን ፤ ኣንዳንዴ ግን በቀጥታ ሾፌሩን ማነጋገር የሚያስፈልግዎት ኣጋጣሚ ለምሳሌ ስለጠፋ እቃ፣ የትምህርት ቤት መጓጓዣና የመግቢያና የመውጫ ኣጠቃቀም ኣስመልክቶ ማነጋገር ይችላሉ።